Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በሞያቸው በማገልገል ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈው ዶ/ር ፍሰሃየ አለምሰገድ የተሰማውን ሃዘን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈው ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የተሰማውን ሃዘን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ባልደረባ የነበሩት ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ህብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያለ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተይዘው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በኋላ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ሚኒስቴሩም ለዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ቤተሰብ እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን ሲል ገልጿል፡፡

Exit mobile version