Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ያላትን አፈጻጸም አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው፡፡

በጋምቢያ ባንጁል እየተካሔደ በሚገኘው ስብሰባ በአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር (ባንጁል ቻርተር) ወቅታዊ የኢትዮጵያ አፈጻፀምና በአፍሪካ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) መነሻ ወቅታዊ አፈጻፀም ላይ የኢትዮጵያ ልዑክ ሪፖርቶችን አቅርቧል፡፡

የፍትሕ ሚኒስትር ዴዔታ በላይሁን ይርጋ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሪፖርት ዘመኑ በቻርተሩና ፕሮቶኮሉ መሠረት ያሉባትን ግዴታዎች ለመወጣትና የሰብዓዊ መብቶችን ከማስጠበቅ አንጻር የተወሰዱ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ እርምጃዎችን የሚመለከቱ ለውጦች ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል።

ሪፖርቱን ተከትሎ ከኮሚሽነሮች ለተነሱ ጥያቄዎች ኢትዮጵያ በልዑካን ቡድኑ አማካኝነት ግንቦት 4 ቀን 2017 ምላሾችን ትሰጣለች ብለዋል፡፡

መድረኩ ኢትዮጵያ በባንጁል ቻርተር እና በማፑቶ ፕሮቶኮል ስምምነቶች መሠረት በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶችን እና የጾታ እኩልነትን ለማጎልበት ያላትን ቁርጠኝነት የምታሳይበት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

Exit mobile version