Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኒውካስል ዩናይትድ ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ቼልሲን 2 ለ 0 በማሸነፍ ደረጃውን አሻሻለ፡፡

በሴንት ጄምስ ፓርክ በተደረገው ጨዋታ ሳንድሮ ቶናሊ እና ቡሩኖ ጉማሬሽ አስቆጥረዋል፡፡

በጨዋታው የቼልሲው አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰን በኒውካስሉ ተከላካይ ሲቬን ቦትማን ላይ በሰራው ጥፋት በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል፡፡

የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስል ነጥቡን ወደ 66 ከፍ በማድረግ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቼልሲ በነበረበት 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

Exit mobile version