Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው 29ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና በየነ ባንጃ እና ተመስገን ብርሃኑ እንዲሁም ማሞ አየለ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸንፎ ወጥቷል።

ወልዋሎ አዲግራት ከሽንፈት ያልታደጉትን ግቦች ፉዓድ አዚዝ (ፍ) እና ዳዋ ሁጤሳ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

Exit mobile version