Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በማዕከሉ አዲስ የዲጂታል ኢንተርፕራይዝ አሠራር መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዲጂታል ኢንተርፕራይዝ የተሰኘ አዲስ አሠራር መሰጠት መጀመሩን የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስቴሩ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መካከል ሁለቱ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መሰጠት መጀመራቸውን ሚኒስትሯ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

አገልግሎቶቹም የውጭ ሀገር ዜጎች የሥራ ፈቃድ እና እድሳት እንዲሁም ዲጂታል ኢንተርፕራይዝ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ዲጂታል ኢንተርፕራይዝ እንደ ሀገር አዲስ ሥርዓት መሆኑን ጠቁመው፤ አገልግሎቱ ዜጎች በኢንተርፕራይዝ ሲደራጁ ይገጥማቸው የነበረውን የተንዛዛ አሠራር ያስቀራል ብለዋል።

ቀደም ሲል በኢንተርፕራይዝ የመደራጀት ሂደቱ የበርካታ ተቋማትን በር ማንኳኳት የሚጠይቅ እና አካሄዱም መጉላላትን ሲያስከትል እንደነበር አውስተዋል፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል ዘመናዊ አገልግሎት አሰጣጥን ከማረጋገጥ በዘለለ ለተቋም ግንባታ አጋዥ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version