Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ18 የገጠር ከተሞች 50 ሺህ ቤቶች አነስተኛ የሶላር ኃይል ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 18 የገጠር ከተሞች 50 ሺህ ቤቶች አነስተኛ የሶላር ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር ስራ አስፈፃሚ ብርሃኑ ወልዱ እንደገለጹት፤ በገጠር የሚኖሩ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።

በዚህም የገጠር አካባቢዎች እና የገጠር ከተሞችን በፀሐይ ኃይል አማካኝነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በ18 የገጠር ከተሞች 50 ሺህ ቤቶች አነስተኛ የሶላር ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዚህ የቤተሰብ ፀሐይ ኃይል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚሆኑ ዜጎች ከመደበኛ የቤት ውስጥ ፍጆታ ባሻገር ለግብርና ሥራ እየተገለገሉበት መሆኑን አቶ ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡

አርሶና አርብቶ አደሩ በነዳጅ እና በጉልበት የሚወጣውን የገፀ ምድር ውሃ፣ በፀሐይ ሀይል እንዲያወጣ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በእየናዳብ አንዱዓለም

Exit mobile version