Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች እስራኤል እሸቱ እና አሊ ሱሌማን ሲያስቆጥሩ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቢኒያም ፍቅሬ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 13 ከፍ በማድረግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ ከተማ በ37 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ሀይቆቹ ተከታታይ ሶስተኛ ድላቸውን ሲያስመዘግቡ ፈረሰኞቹ በበኩላቸው ባለፉት ተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል፡፡

Exit mobile version