አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሂደት የተካተቱ አገልግሎቶችን የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።
ኢኮኖሚ ልዩ ዞኑ መዋዕለ ንዋያቸውን በአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማፍሰስ ፍቃደኛ ከሆኑ አምስት ሀገር በቀል እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ስምምነት ፈፅሟል።
በመንግሥት እና የግል አጋርነት የሚመራው የኢኮኖሚ ልዩ ዞኑ የአፓርትመንት ቤቶች ሽያጭ ያስጀመረ ሲሆን፤ በምዕራፍ አንድ የግንባታ ሂደቱ አፓርትመንት እንዲሁም የንግድ ተቋማትን አጣምሮ በ45 ሺህ ሜትር ስኩዌር ስፍራ ላይ ይገነባል።
አዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለመዲናዋ አዲስ ገፅታ የሚያላብስ፣ ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ እና ተጨማሪ የውበት ምንጭ ይሆናል ነው የተባለው፡፡
በአዲስ አበባ ጎተራ አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው አዲስ ቱሞሮ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን የምዕራፍ አንድ ሥራውን በቀጣይ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ በማስቀመጥ ማስጀመራቸው ይታወሳል፡፡
በሚኪያስ ዓለሙ