አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኤፍኤ ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ ዛሬ ምሽት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
የፍጻሜ ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በእንግሊዝ ዌምብሌይ ስታዲየም ነው የሚካሄደው፡፡
ውሃ ሰማያዊዎቹ ለ8ኛ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ የሚገቡ ሲሆን÷ክሪስታል ፓላሶች ደግሞ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የኤፍኤ ካፕ ዋንጫን ለማንሳት ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
ማንቼስተር ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ከክሪስታል ፓላስ ጋር በተገናኘባቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት አላስተናገደም።
ዋንጫውን ለሰባተኛ ጊዜ ማንሳት የቻሉት ሰማያዊዎቹ ናታን አኬ፣ ጆን ስቶንስ እና ሮድሪ በጉዳት ለጨዋታው እንደማይደርሱላቸው አስታውቀዋል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ ባለፈው ዓመት በኤፍኤ ካፕ ውድድር ለፍጻሜ ደርሶ በማንቼስተር ዩናይትድ መሸነፉ ይታወሳል።
በዮናስ ጌትነት