Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያን ለማዘመን የተጀመሩ ሥራዎች የአመራሩን የለውጥ ቁርጠኝነት ያሳያሉ – በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያን ለማዘመን የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች የአመራሩን ሙያዊ ብቃትና የለውጥ ቁርጠኝነት አመላካች መሆናቸውን በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስታይን ክሪስተንሰን ገለጹ።

አምባሳደሩ በቆይታቸው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ሀገራቱ የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ትብብር እንዳላቸው የገለጹት አምባሳደሩ÷ በተለይም በጤና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ሌሎች መስኮች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ እያሳየች ያለውን ዘርፈ ብዙ ለውጥ አድንቀው÷ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች የአመራሩን ሙያዊ ብቃትና የለውጥ ቁርጠኝነት አመላካች ናቸው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትሮችና በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሃላፊዎች ለሥራ ባላቸው ትጋት መደነቃቸውን ገልጸዋል።

ሀገሪቱ የሙያዊ ብቃትና የሥራ ተነሳሽነት ያላቸው ዜጎች ያሏት ውብ ሀገር እንደሆነች እና ኢትዮጵያ ውስጥ በመስራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ኖርዌይ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ትብብራቸውን የበለጠ ለማሳደግ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው እየሰሩ እንደሆነ መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version