አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይናው ሁዋጂያን ኢንተርናሽናል ላይት ኢንዱስትሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ምርቶችን በኢትዮጵያ ለማቅረብ የሚያስችለውን አዲስ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከፍቷል።
በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በዚህ ወቅትም ሁዋጂያን በአዲሱ ቢሮ በዓለም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራችነት ቀዳሚ ከሆኑ ኩባንያዎች አንዱ የሆነውን የቻይናው ጓንግዙ አውቶሞቢል ኩባንያ ምርቶች እንደሚያቀርብ ተገልጿል።
የሁዋጂያን ሃላፊ ዛንግ ሁዋሮንግ ÷ኢትዮጵያ ያላትን ምቹ የኢንቨስትመንት አመራጭ በመጠቀም በአፍሪካ ቀዳሚና በገበያው ተመራጭ ለመሆን በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
ኩባንያው እያደገ በመጣው የኢትዮጵያ ገበያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በስፋት ለማቅረብ ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በአሸናፊ ሽብሩ