Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል በመኸር እርሻ ከ5 ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት ታረሰ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017/18 የመኸር ወቅት በዘር ለመሸፈን ከታቀደው 10 ነጥብ 8 ሚሊየን ሔክታር እስከ አሁን 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ሔክታሩ መታረሱን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡

እስከ አሁን ከታረሰው ውስጥም 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ሔክታሩ ትራክተር በመጠቀም የተከናወነ መሆኑን በቢሮው የሰብል ልማት ዳይሬክተር ሙስጠፋ ሁሴን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

በመኸር ወቅት ለማረስ ከታቀደው 80 በመቶውን በኩታገጠም ለማረስ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የበቆሎ እና ማሽላ ሰብሎችን የመዝራት ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ መታቀዱን እና ከ6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ወደ ክልሉ ገብቶ ለአርሶ አደሩ በመከፋፈል ሂደት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የተለያዩ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደ ክልል 11 በሚሆኑ ሰብሎች ላይ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡

በዮናስ ጌትነት

Exit mobile version