Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

 ፕሬዚዳንት ፑቲን ሩሲያ ለተኩስ አቁምና ለሰላም ንግግር ዝግጁ መሆኗን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከኢስታንቡሉ ድርድር ማግስት በስልክ ተወያይተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቶቹ ሁለት ሰዓታትን በፈጀው ውይይታቸው÷ ሩሲያ እና ዩክሬንን ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮ ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ውይይቱ ውጤታማና ጠቃሚ እንደነበር የገለጹ ሲሆን÷ ዋሺንግተን ሞስኮ እና ኪየቭን  ለማሸማገል የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

ሩሲያ የተኩስ አቁም ለማድረግና ከዩክሬን ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ÷ሞስኮ ወደ ሰላም ስምምነት የሚወስደውን አማራጭ ትከተላለች ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸው÷ በሩሲያ እና ዩክሬን የሰላም ድርድር ሒደት ውስጥ አሜሪካ ያላትን አቋም ለፕሬዚዳንት ፑቲን ማስረዳታቸው ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው  ውይይት በኋላ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር ተመሳሳይ የስልክ ውይይት እንደሚያደርጉ መጠቆሙን አር ቲ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version