አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለ3 ሺህ 351 ተሽከርካሪዎች ከ850 ሚሊየን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑት ተሽከርካሪዎችም፤ 1 ሺህ 153 አገር አቋራጭ አውቶቡሶች፣ 1 ሺህ 716 የከተማ አውቶቡሶችና 482 የፐብሊክ ሰርቪስ አውቶቡሶች መሆናቸው ተብራርቷል፡፡
በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራትም ከ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ በዲጂታል የነዳጅ ግብይት መካሄዱን ሚኒስቴሩ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ፤ ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ወዲህ ከ136 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ በዲጂታል የነዳጅ ግብይት ተከናውኗል፡፡
በመሳፍንት እያዩ