አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ የዓሣ ሀብትን ለመጠበቅ የሚያስችል የአሥተዳደር መመሪያ በቅርቡ ጸድቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
መመሪያው በግድቡ ያለውን የዓሣ ምርት አሰባሰብ ሥርዓት በማስያዝ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል መሆኑን በሚኒስቴሩ የዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ኃላፊ ፋሲል ዳዊት (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በግድቡ ዓሣ ለማምረት የሚፈልጉ አካላት ተገቢውን ቁሳቁስ እንዲጠቀሙ የሚያስገድድ መመሪያ መሆኑን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
ከአሁን በፊት በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ውስጥ በሚገኙ የዓሣ ዝርያዎች ላይ የተከሰቱ ችግሮች እንዳይፈጠሩ መመሪያው መዘጋጀቱ ወሳኝ ድርሻ አለው ብለዋል።
በሰለሞን ይታየው