Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፈር ማዳበሪያን በራስ አቅም ማምረት ሀገርን ከብዙ ችግሮች ይታደጋል- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ለማምረት የተያዘው ዕቅድ ኢትዮጵያን ከብዙ ችግሮች እንደሚታደግ እና ምርታማነትን እንደሚያሳድግ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ገለጹ፡፡

መንግሥት ይፋ ያደረገው የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ የማምረት ዕቅድ፤ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚላይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ መሆኑንም ምሁራኑ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው አቡሌ መሀሪ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ ማምረት የሀገርን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ እርምጃ ነው።

የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥማምረት ከተቻለ የኢትዮጵያ ግብርናን እስከ አሁን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከፍያለ ምርት እንዲያስገኝ ዋስትና ይሆናል ያሉት ደግሞ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪው አረጋ ሹመቴ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

ሀገር ውስጥ ማምረቱ ለነገ የማይባል እና ልክ እንደ ሕዳሴ ግድብ በዘመቻና የራሱ ኢኒሼቲቭተቀርፆለት ሊሠራበት እንደሚገባም መክረዋል፡፡

በዙፋን ካሳሁን

Exit mobile version