አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት 10 ወራት 151 መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መሥተዳደድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት በሚል መሪ ሐሳብ የኢንዱስትሪዎች ምርት ኤግዚቢሽን በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ በዚሁ ወቅት፤ 017 በጀት ዓመት በክልሉ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን እና ባለፉት 10 ወራት 151 መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸዋል፡፡
ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች ከ56 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የኢንቨስትመንት ተግባር ከነበረበት ወደ 59 በመቶ ከፍ ብሏል፤ ይህም ኢትዮጵያውያን ማምረት እንደሚችሉ በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል።
በሌላ በኩል በደብረ ብረሃን ከተማ አሥተዳደር ለ510 ወገኖች ሥራ ዕድል የፈጠሩ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ሦስት ፕሮጀክቶች ለአገልግት ክፍት መሆናቸውን የአሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ተናግረዋል፡፡
ከተማ አሥተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ 20 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ እንዲገቡ ማስቻሉንም ተቅሰዋል፡፡
በእታገኝ መኮንን