Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ221 ሺህ በላይ ሰዎች ለፋይዳ መታወቂያ ተመዘገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጀመረው የፋይዳ መታወቂያ ንቅናቄ ባለፉት 61 ቀናት ከ221 ሺህ በላይ ሰዎች የፋይዳ መታወቂያ ማግኘት የሚያስችላቸውን ምዝገባ አከናወኑ፡፡

በየደረጃው በሚገኙ የክልሉ አደረጃጀቶች የፋይዳ መታወቂያን አስፈላጊነት አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ዋና አማካሪ እና ልዩ ረዳት ንጉሴ አስረስ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

ወደ ምዝገባ ቦታ የሚመጡ ተመዝጋቢዎችም ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል፡፡

ፋይዳ አሁን ላይ ለተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን እና የፋይዳ ጉዳይ የቴክኖሎጂ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ መታወቂያውን እንዲያወጣ አሳስበዋል፡፡

እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 850 ሺህ ምዝገባ ለማከናወን ማቀዳቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በወንድማገኝ ፀጋዬ

Exit mobile version