Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት ይካሄዳሉ።

ሊቨርፑል አሸናፊነቱን አስቀድሞ ባረጋገጠበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ38ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት ምሽት 12፡00 ላይ ይደረጋሉ።

በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ሻምፒዮኑ ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ፣ ፉልሃም ከማቼስተር ሲቲ፣ ማቼስተር ዩናይትድ ከአስቶን ቪላ፣ ኒውካስትል ከኤቨርተን፣ ኖቲንግሃም ከቼልሲ፣ ሳውዛሀፕተን ከአርሰናል ይገናኛሉ።

በሊጉ በጠባብ የነጥብ ልዩነት የሚበላለጡት እና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ዕድል ያላቸው ማንቼስተር ሲቲ፣ ኒውካስል፣ ቼልሲ፣ አስቶን ቪላ እና ኖቲንግሃም ፎረስት ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሊቨርፑል እና አርሰናል የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊነታቸውን አስቀድመው ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው።

እንዲሁም እኩል 13 ጊዜ መረባቸውን ሳያስደፍሩ በመውጣት ለወርቅ ጓንቱ የሚፎካከሩት የኖቲንግሃሙ ማትዝ ሰልስ እና የአርሰናሉ ዴቪድ ራያ በራቸውን ላለማስደፈር ወደ ሜዳ ይገባሉ።

በዮናስ ጌትነት

Exit mobile version