Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማረሚያ ቤቶች ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተሻሽሏል – ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በማረሚያ ቤቶች ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ተሻሽሏል ብለዋል።

ኮሚሽነሩን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤትን ጎብኝተዋል።

ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በ2017 ዓ.ም በ61 ማረሚያ ቤቶች ላይ ቅኝት አድርጓል።

በዚህም ለታራሚዎች የሚቀርበው ቀለብ አለመሻሻልና ከክልል ክልል መለያየት እንዲሁም የይቅርታ እና ምህረት አሰጣጥ ወጥ አለመሆን በማረሚያ ቤቶች የታዩ ችግሮች መሆናቸውን አንስተው÷ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኙም አሳስበዋል።

ኮሚሽኑ ከጉብኝቱ በኋላ የተመለከታቸውን ጨምሮ በክልሎች ባደረጋቸው ቅኝቶች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በሪፖርቱም በማረሚያ ቤቶች ያለው የታራሚዎች የሰብዓዊ መብት አያያዝ መሻሻሉን እና የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተመላክቷል።

በሲሳይ ወርቁ

Exit mobile version