Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ዮሀንስ ደረጀ እና እስማኤል አብዱል ጋንዩ ሲያስቆጥሩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ቢንያም ካሳሁን ከመረብ አሳርፏል፡፡

ድሬዳዋ ከተማ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ሲያሳካ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ39 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ድሬዳዋ ከተማ በተመሳሳይ 39 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

Exit mobile version