Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ የተገነቡት ስታዲየሞች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገቢ በሶማሌ ክልል ጎዴ፣ ደገሃቡር፣ አራርሶ እና ጅግጅጋ ከተሞች አራት መለስተኛ ስታዲየሞች ግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡

በጎዴ እና ደገሃቡር የሚገነቡት ስታዲየሞች አፈጻጸም 80 በመቶ መድረሱን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሁሴን ቃሲም (ዶ/ር) ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም በአራርሶ እና ጅግጅጋ የተገነቡት ስታዲሞች ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመደመር መጽሐፍ ሽያጭ ገቢን ለራሳቸው ጥቅም ማዋል ሲችሉ ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውል ስለፈቀዱ በክልሉ ሕዝብና መንግሥት ስም ሁሴን ቃሲም (ዶ/ር) ምሥጋና አቅርበዋል።

ይህ አርዓያነት ያለው ተግባር ለሌሎች አመራሮች በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በአጠቃላይ ለስታዲየሞቹ ግንባታ የሚያስፈልገው የገንዘብ መጠንም 146 ሚሊየን 903 ሺህ 268 ብር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version