Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአቮካዶ ኢኒሼቲቭ የተሻለ ውጤት እየታየበት ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአቮካዶ ኢኒሼቲቭ ጅምር ላይ ቢሆንም የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ ነው አለ ግብርና ሚኒስቴር፡፡

በሚኒስቴሩ የሆልቲካልቸር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ አብደላ ነጋሽ እንዳሉት፤ እየተተከሉ ከሚገኙ የፍራፍሬ ችግኞች መካከል አቮካዶ እስከ 80 ከመቶ ድርሻ አለው።

በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ክልሎች የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎች በኩታ ገጠም እና በመስኖ በስፋት በመመረት ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡

ለኢኒሼቲቩ ውጤታማነት የአረንጓዴ ዐሻራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰው፤ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ለዘርፉ የፋይናንስ ድጋፍ መደረግ እንደሚጀምር ጠቁመዋል፡፡

ባለፉት 10 ወራት በጥሬው እና ተቀነባብሮ ከተላከ የአቮካዶ ምርት ከ2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር በላይ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

በአልማዝ መኮንን

Exit mobile version