Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 በእንሰት ላይ የተደረገው ምርምር ውጤታማ ሆኗል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እንሰት በቆላማ የአየር ፀባይ መልማት እንዲችል የተደረገው ምርምር ውጤታማ ሆኗል አለ የደቡብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት።

እንሰትን ከቆላማ አካባቢዎች ጋር በማላመድ ከፍተኛ ፀሐይ አግኝቶ በአጭር ጊዜ ብዙ ምርት እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉ በጥናት መረጋገጡን የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር አብዮት መብራቴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የአረካ ግብርና ምርምር ማዕከል በቆላማ አካባቢዎች ባደረገው ምርምር በሁለት ዓመት ከግማሽ ውስጥ መድረስ የሚችል የእንሰት ዝርያ ማሻሻሉን አሳውቀዋል።

ኢንስቲትዩቱ ሀገር በቀል ሰብሎች ከፍተኛ ምርት እንዲሰጡ ዝርያ የማሻሻል ሥራ የሚያከናውኑ አምስት የምርምር ማዕከላት እንዳሉትም ገልፀዋል፡፡

ተቋማቸው በእንሰት ዙሪያ የሠራው ጥናት በምርት መጠንና የሚበቅልበትን ሥነ-ምኅዳር በመለየት ረገድ አዲስ ግኝት ማምጣቱንም ነው የጠቀሱት፡፡

እንሰት አሁን ከሚበቅልበት ሥነ-ምኅዳር ውጭ ለማላመድ የሚያስችል ምርምር በልዩ ትኩረት እያከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የአረካ ግብና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ገነነ ገዛኸኝ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በመለሰ ታደለ

Exit mobile version