Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ33ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ ስሑል ሽረን 5 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በጨዋታው ለሐዋሳ ከተማ አሊ ሱሌማን አራት ግቦችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ጎል ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ አሳርፏል፡፡

የሐዋሳ ከተማው የፊት መስመር ተጫዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 19 በማድረስ የሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት መምራቱን ቀጥሏል፡፡

እንዲሁም ስሑል ሽረን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ብርሃኑ አዳሙ አስቆጥሯል፡፡

ሐዋሳ ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያሳካ ስሑል ሽረ ሶስተኛ ተከታታይ ጨዋታውን ተሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ሐዋሳ ከተማ በ44 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ስሑል ሽረ በ22 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ቀን 9 ሠዓት መቐለ 70 እንደርታ ከሲዳማ ቡና እንዲሁም ምሽት 12 ሠዓት ላይ ላይ ፋሲል ከነማ ከወላይታ ድቻ ይገናኛሉ፡፡

Exit mobile version