Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሕዝበ ሙስሊሙ ለሀገር ሰላም እና አንድነት መትጋት ይጠበቅበታል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 1 ሺህ 446ኛው ዓመተ ሂጅራ ዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሐዋሳ እየተከበረ ነው፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በሚሊኒየም ዐደባባይ በመሰባሰብ የሶላት ሥነ-ሥርዓት አከናውኗል፡፡

የሲዳማ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱል ሻኩር አብዱል ቃድር በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ዒድ አል አድሃ የዕርድ በዓል በመሆኑ ሕዝበ ሙስሊሙ ያረደውን ሳይሰስት ለተቸገረ በማካፈል የአላህን ትዕዛዝ ሊፈፅም ይገባል ብለዋል።

የእምነቱ ተከታዮች ሐይማኖታዊ ሥርዓቱን ከመተግበር ጎን ለጎን ለሀገር ሰላምና አንድነት መፀለይ እንዲሁም መሥራት እንደሚገባቸውም መልዕክት ተላልፏል፡፡

በመቅደስ አስፋው

Exit mobile version