Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፋር ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሚወስዱ ተማሪዎች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል ከ44 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 4 ሺህ 893 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሁመድ አብደላ ለፋና ዲጂታል እንደገለጹት፤ በአጠቃላይ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከሚወስዱት መካከል 4 ሺህ 99 ተማሪዎች ፈተናቸውን በወረቀት ይወስዳሉ፡፡

እንዲሁም በኦንላይን የሚፈተኑት ደግሞ 794 መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በሠመራ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዩኒቨርሲቲው በበይነመረብ ለሚሰጠው ፈተና ግብዓት ማሟላቱን አረጋግጠዋል፡፡

የማካካሻ ትምህርትን ጨምሮ ተከታታይ ሞዴል ፈተናዎች እና የኦንላይን ሁኔታውን በተመለከተ ስልጠና ለተማሪዎች እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በፈተና ወቅት እንዳይቸገሩ በሥነ-ልቦና እንዲዘጋጁ ያግዛል ብለዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version