Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሲዳማ ቡና ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የ2017 የኢትዮጵያ ዋንጫ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸንፏል።

የሲዳማ ቡናን ግቦች ሀብታሙ ታደሰ እና መስፍን ታፈሰ ሲያስቆጥሩ የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ ካርሎስ ዳምጠው ከመረብ አሳርፏል።

ሲዳማ ቡና የዋንጫው ባለቤት መሆኑን ተከትሎ በቀጣዩ ዓመት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል።

Exit mobile version