አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ34ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቢንያም በላይ የሀዋሳ ከተማን ማሸነፊያ ግብ አስቆጥሯል።
ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ እና ኢትዮጵያ ቡና 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
የሊጉ መርሐግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሀድያ ሆሳዕና ይገናኛል።
በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረገ ሌላ መርሃ ግብር ሀድያ ሆሳዕና በፀጋዓብ ግዛው ብቸኛ ጎል ንግድ ባንክን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook WMCC
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!