አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በኦንላይን እንዲፈተኑ ለማስቻል አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ ነው አለ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ፡፡
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በአዲስ አበባ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለመውሰድ 51 ሺህ 521 ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡
ተማሪዎቹ በቀን፣ በማታ እና በርቀት መርሐ ግብር ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንዲሁም የመከላከያ እና የግል ተፈታኞች ናቸው ብለዋል፡፡
የ2017 ዓ.ም ሁሉም የመዲናዋ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን እንደሚወስዱ ጠቁመው÷ ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን በትክክል እንዲወስዱ የሚሰጠው ልምምድ እየተጠናቀቀ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡
ተፈታኞች ለፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ የተለያዩ ሞዴል ፈተናዎችን እንደወሰዱ የተናገሩት አቶ ዲናኦል÷ በሥነ ልቦና ረገድም አስፈላጊው ምክር መሰጠቱን አመልክተዋል፡፡
ተማሪዎች በቀረው ጊዜ ውስጥ ለፈተናው የሚያደርጉትን ዝግጅት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!