Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የምሁራን ሚና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገራዊ ምክክር ሂደት ምሁራን እና የሀሳብ መሪዎች ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

ሀገራዊ ምክክሩ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ የምሁራን ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በምክክሩ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የምሁራን ሚና የላቀ መሆኑን አስገንዝቧል።

ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ ላይ ከምሁራን ግብዓት ለማሰባሰብ እና ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ለመመካከር ያዘጋጀው መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም እንዳሉት፤ የምክክር ሂደቱ በሀገር ደረጃ ለሚጠበቁ እና እጅግ ለሚያስፈልጉ ውጤቶች የምሁራን ሚና ከፍተኛ ነው።

ሀገራዊ ምክክሩ አሁን ከደረሰበት ደረጃ አኳያ የምሁራን እና የሀሳብ መሪዎች ሚና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል።

ኮሚሽኑ ምሁራን በቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ላይ ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version