Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) እድሳት ተደርጎለት ላለፉት 4 ወራት በሙከራ ስራ ላይ የቆየው የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡

ቤተመንግስቱ ጥንታዊ ተሽከርካሪዎችና መካነ እንስሳትን ጨምሮ በውስጡ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን፥ ደረጃቸውን የጠበቁ ሬስቶራንቶችና ስፓዎች ይገኙበታል፡፡

ሙዚየሙ ክፍት መደረጉን አስመልክተው የብሔራዊ ቤተመንግስት ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ደሬሳ በሰጡት መግለጫ፥ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ለማላቀቅ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡

የብሔራዊ ቤተመንግስቱ ሙዚየም ከማክሰኞ በስተቀር ሳምንቱን ሙሉ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 11:30 ለህዝብ ክፍት ይሆናል ብለዋል፡፡

ከጎብኚዎች የሚገኘው ገቢ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ቀሪ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ያግዛል ተብሏል፡፡

የመግቢያ ዋጋ መደበኛ 3 መቶ ብር እንዲሁም ለልዩ ትኬት 1 ሺህ ብር መሆኑንም ነው አቶ ምትኩ የገለጹት፡፡

በዘረዓያዕቆብ ያዕቆብ

Exit mobile version