Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሜሪካ ጣልቃ የምትገባ ከሆነ ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል- አያቶላህ አሊ ሀሚኒ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን እና እስራኤል ግጭት አሜሪካ ወታደራዊ ተሳትፎ ካደረገች ከፍተኛ አደጋ ሊከሰት ይችላል ሲሉ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ አስጠነቀቁ፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ እንድትስጥ ማሳሰባቸውን ተከትሎ የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሀሚኒ ሀገራቸው በቀላሉ የምትንበረከክ እንዳልሆነች ማስታወቃቸውን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የኢራን እስራኤል ግጭት ኢራን 400 የሚደርሱ ባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል በመተኮስ በቴል አቪቭ እና ሀይፋ ከተሞች የሚገኙ ህንጻዎች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ማድረሷ ይታወቃል፡፡

እስራኤል በበኩሏ በቀጠለችው የአየር ጥቃት የኢራን የኒውክለር ጣቢያዎችን ጨምሮ የሀገሪቱ ወሳኝ ተቋማት ማውደሟን ቀጥላለች፡፡

የሁለቱ ሀገራት ግጭት እየተባባሰ በመሄዱ በቴህራን እና ቴል አቪቭ በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል፡፡

በአቤል ንዋይ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version