Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በ30 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን የመማሪያ ክፍሎች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በ30 ሚሊየን ብር ወጪ በቡሬ ከተማ የዕድገት በህብረት መጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስገነባቸውን 15 የመማሪያ ክፍሎች አስረከበ።

በ1971 ዓ.ም የተመሰረተው ትምህርት ቤቱ፤ በዕድሜ ብዛት የመማሪያ ክፍሎቹ ፈራርሰው ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ አልነበሩም።

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አበበ አለማየሁ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የመማሪያ ክፍሎችን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ባለ ሁለት ወለል 15 የመማሪያ ክፍሎች አስገንብተው አስረክበዋል።

የፌቤላ ኢንዱስሪያል ተወካይ ኃላፊ አቶ ዳዊት ገ/ስላሴ በበኩላቸው፤ ፊቤላ ኢንዱስትሪያል በከተማዋ ከፈጠረው የሥራ እድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር በተጨማሪ ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለዚህም የቡሬና አካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ወጭ አድርጓል ነው ያሉት።

የዕድገት በህብረት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ 30 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉን ገልጸው፤ ለሁሉም ክፍሎች ደረጃውን የጠበቀ ወንበርና ጠረጴዛ አሟልቷል ብለዋል።

የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፊቤላ ኢንዱስትሪያል የሥራ ባህል እንዲስፋፋና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ከማድረግ ባለፈ ማህበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ አርአያነት እንዳለው ገልጸው፤ ምስጋና አቅርበዋል።

በላይነህ ክንዴ ግሩፕ በፋውንዴሽኑ አማካኝነት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ባለፉት አራት ዓመታት ከ900 ሚሊየን ብር በላይ ለማህበራዊ ኃላፊነት ወጪ አድርጓል።

የፍጻሜ ምዕራፍ ላይ ለሚገኘው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ የሚውል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰጠኝ እንግዳው ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version