አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እየተከናወነ ባለው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የወተት ምርታማነት እያደገ መጥቷል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት፤ በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ተጠቃሚ ሆነዋል።
የወተት ምርታማነትን ለመጨመር በተሰጠው ልዩ ሀገራዊና ክልላዊ ትኩረት የአምራቾች ቁጥር መጨመሩንና የወተት ምርት ማደጉን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በዓመት ይመረት የነበረው 325 ሚሊየን ሊትር ወተት አሁን ላይ ወደ 650 ሚሊየን ሊትር ደርሷል በማለት ገልጸው፤ በዚህም የክልሉ የወተት ምርታማነት በእጥፍ ማደጉን ጠቁመዋል።
በክልሉ ውስጥ ስምንት የወተትና ወተት ተዋጽኦ ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች መገንባታቸውን ገልጸው÷ ስድስቱ ስራ መጀመራቸውንና ቀሪዎቹ በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንዲገቡ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
ኢንዱስትሪዎቹን ከ2 ሺህ 600 በላይ የሚደርሱ ዜጎች በሕብረት ስራ ማህበር ተደራጅተው በመገንባት ስራ መጀመራቸውንና ይህም አርሶ አደሩ በገጠር የኢንዱስትሪ ባለቤት እንዲሆኑ ያስቻለ መሆኑን ነው ያስረዱት።
የወተት ምርታማነትን ለማሳደግና ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ እንደሆነም ለፋና ዲጂታል ጠቁመዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረውን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመጓዝ ግቦችን በማሳካት በምግብ ራስን የመቻል እና ሥርዓተ ምግብን ማሻሻል እውን ከማድረግ አንጻር ተስፋ ሰጪ እንደሆነም ነው ያነሱት።
በተጨማሪም የወተት ምርታማነቱ በእንስሳት ጤና እና ዝርያ ማሻሻል እንዲሁም መኖ ልማት ላይ በተሰሩ ውጤታማ ስራዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ተናግረዋል።
በአድማሱ አራጋው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!