አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የእስራኤል እና ኢራን ግጭት በእርግጠኝነት መፍትሄ ይገኝለታል አሉ፡፡
አንድ ሳምንት ያስቆጠረውን የእስራኤል እና ኢራን ግጭት ለማስቆም ሩሲያ ከሀገራቱ ጋር ንግግር እያደረገች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሴንት ፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ላይ እንዳሉት፥ ሞስኮ ግጭቱን ለመፍታት ባቀረበቻቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
የእኛ ፍላጎት ሀገራቱን ማደራደር ሳይሆን የሰላም አማራጮችን ማቅረብ ያሉት ፕሬዚዳንት ፑቲን፤ በሁለቱም ወገኖች ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!