አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል ጀርመናዊውን የአጥቂ አማካይ ፍሎሪያን ቪርትስ የክለቡ የዝውውር ክብረ ወሰን በሆነ ዋጋ ከባየር ሊቨርኩሰን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል።
ሊቨርፑል ለተጫዋቹ ዝውውር 100 ሚሊየን ፓውንድ እና ተጨማሪ 16 ሚሊየን ፓውንድ የሚከፍል ሲሆን፥ ለአምስት አመት በአንፊልድ የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።
ፍሎሪያን ቪርትስ ለቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን 197 ጨዋታዎችን በማድረግ 57 ግቦችን አስቆጥሯል።
የ22 አመቱ ቪርትስ ለቀዮቹ ፊርማውን ካኖረ በኋላ በሰጠው አስተያየት፥ ለረዥም ጊዜ ስጠብቀው የነበረው ዝውውር በመሳካቱ ደስተኛ ነኝ ብሏል።
በኃይለማርያም ተገኝ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!