አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ወጣት አብዱሰላም መሐመዳሚን የአጋሮ ከተማ ነዋሪ ነው፡፡ በ2005 ዓ.ም ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ትምህርት ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቋል። ከተመረቀ በኋላ ባጋጠመው የነርቭ ህመም ድንገት ሁለቱም እግሮቹ መራመድ ተሳናቸው።
ያጋጠመው የአካል ጉዳት ተስፋ አስቆርጦት ለስኬቱ እንቅፋት እንዲሆን ያልፈቀደው ወጣቱ÷ ይበልጥ ብርታት አጎናጽፎት ሁለተኛ ዲግሪውን ጀምሯል፡፡
በሕይወቱ የገጠመውን ፈተና በፅናት ተቋቁሞ ለማለፍ እና ሰርቶ ኑሮውን ለማሸነፍ በዊልቸር ላይ ተቀምጦ የሚሰራውን ሥራ ሲያሰላስል የሞባይል ጥገና ሙያን ምርጫው አደረገ።
በቤተሰቦቹ ድጋፍ የሞባይል ጥገና ሙያ ተምሮ በትውልድ ቀየው አጋሮ ከተማ ሥራውን በመጀመር ከራሱ አልፎ ቤተሰቦቹን እያስተዳደረ ይገኛል።
“እግሬ እንጂ መራመድ ያቃተው አዕምሮዬ ብሩህ ነው፤ እጆቼም ይሰራሉ” ይላል።
የሁለተኛ ዲግሪውን በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሳምንታዊ መርሐ ግብር በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ትምህርት ዘርፍ ተከታትሎ ለመመረቅ በቅቷል።
ያጋጠመው የአካል ጉዳት ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ብርታትን እንዳጎናፀፈው በልበ ሙሉነት ይናገራል፡፡
ከሞባይል ጥገናው ባሻገር በተመረቀበት ሙያ ለአካባቢው ነዋሪዎች ነፃ የሥነ ልቦና ማማከር አገልግሎት በፈቃደኝነት እየሰጠ ይገኛል።
የሚያውቁት የአካባቢው ነዋሪዎችም አብዱሰላም ለበርካቶች አርዓያ የሆነ ወጣት ስለመሆኑ ይመሰክራሉ።
አብዱሰላም በተማረበት ሙያ ሕብረተሰቡን እያገለገለ የራሱን የግል ሥራ የማስፋፋት እቅድ ሰንቆ እየሰራም ይገኛል፡፡
በወርቃፈራው ያለው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!