አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጅማ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ይገኛሉ፡፡
አርሲ ዩኒቨርሲቲ 1 ሺህ 201 ተማሪዎችን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ እያስመረቀ ሲሆን÷ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር)፣ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ፍቃዱ ምትኩ (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብሮች አስመርቋል።
በዚህም በመጀመሪያ ዲግሪ 2 ሺህ 53 ተማሪዎች፣ በሁለተኛ ዲግሪ 992 ተማሪዎች እና በሦስተኛ ዲግሪ 61 ተማሪዎችን እንዲሁም ሁለት ተማሪዎች ደግሞ በሰብ ስፔሻሊስት ዲፕሎማ ፕሮግራም ተመርቀዋል።
በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው ከተባበሩት አረብ ኢሜሬቶች ፋጢማ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ምሩቃን ማካተቱ ልዩ ያደርገዋል፡፡
ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩት የትምህርት ዘርፍ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉም ጥሪ ቀርቧል፡፡
በኦሊያድ በዳኔ እና በርስ ኃይለማሪያም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!