አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል አሉ የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሌሊሴ ነሜ፡፡
“ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ” በሚል መሪ ሃሳብ ሁለተኛው ዙር አስተዳደር አቀፍ የአካባቢ ብክለት መከላከል ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ተካሂዷል፡፡
ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት÷ የአካባቢ ብክለት አሁን ላለው የጤና እክል ዋነኛ መንስኤ መሆኑን ገልጸው፤ ብክለቱን ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው÷ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም ላይ ተጽዕኖ እያሳደረ ባለበት በዚህ ወቅት ለአካባቢ ጥበቃና ለጽዱ ኢትዮጵያ ልዩ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል፡፡
አረንጓዴ አሻራ ለድሬዳዋ ከተማ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በምንያህል መለሰ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!