Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በክልሉ በቀጣይ 90 ቀናት በየዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል ይሰራል – ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በቀጣይ 90 ቀናት ሊከናወኑ በታቀዱ ስራዎች የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ በቀጣይ 90 ቀናት በተለይም ለገጠር ኮሪደር ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት በከተማውና በጀጎል ዓለም አቀፍ ቅርስ የተከናወኑ ውጤታማ ስራዎችን ለመድገም ይሰራል ብለዋል።

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሕብረተሰቡ ፈጣን፣ ፍትሃዊና ጥራት ያለውን አገልግሎት እንዲያገኝ ለማስቻል ርብርብ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

የግብርና ልማት ስራዎችን በማጠናከር ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የኑሮ ውድነት ጫናን ለማቃለል መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ውጤታማነት፣ የፅዳትና ውበት ስራዎች ማጎልበት፣ ገቢን ማሳደግና የስራ እድል ፈጠራ የበለጠ ማጎልበት የ90 ቀናት ውስጥ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸውን አብራርተዋል።

የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ውጤታማ ማድረግ ሌላው የርብርብ ማዕከል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዚህም አመራሩ በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version