አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ185 ሚሊየን ብር ወጪ በአርቲስት እንየ ታከለ የተገነባውና የጎንደርን ታሪክ የሚመጥን የባህል ምሽት ቤት ተመርቋል።
የባህል ምሽት ቤቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማይ ልጅ ዓለምና የክልል ሥራ ኃላፊዎች መርቀው ከፍተዋል።
በጎንደር ከተማ በርካታ ሆቴሎች ቢኖሩም ደረጃውን የጠበቀ ለእንግዶች አገልግሎት መስጠት የሚችል የባህል ምሽት አልነበረም ያሉት አቶ ግርማይ÷ አሁን ግን አርቲስት እንየ ታከለ ይህን እውን አድርጋለች ብለዋል።
የቱሪዝም ማዕከል የሆነችውን ጎንደር ለማጉላት መሰል የባህል ምሽት ቤቶችን ለማስፋት ይሰራልም ነው ያሉት።
የእስክስታዋ ንግስት እንየ ታከለ የባህል ምሽት ቤቱ የኢትዮጵያ መልክን ይዞ እንደተሰራ ተናግራለች።
የጎንደር ከተማና የአካባቢውን ባህል ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ያለችው አርቲስት እንየ÷ በተወለድኩበት አካባቢ የዘመናት ህልሜ በመሳካቱ ደስተኛ ነኝ ብላለች።
18 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች ያሉት የባህል ምሽት ቤቱ ለ95 ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል።
በከተማዋ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል የማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት በአርቲስት እንየ ታከለ እየተገነባ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።
በምናለ አየነው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!