አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አካል ጉዳተኝነት ወጣት ኢሞታ ቡኤሳን የሕግ ባለሙያ ከመሆን አላገደውም፡፡ በፈተናዎች ያልተበገረው ፅናቱ ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ዘርፍ እንዲመረቅ አስችሎታል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ተወልዶ ያደገው ወጣት ኢሞታ ቡኤሳ ከትምህርት ይልቅ ለልመና እንዲሰማራ ብዙ ጫናዎች የደረሰበት ቢሆንም በዓላማ ፅናቱ የሕግ ባለሙያ ሆኗል።
ሁለቱንም እግሮች በተፈጥሮ ያጣው ኢሞታ ገና እንደተወለደ “ገፊ” ነው በሚል አጉል ባህል የሞት ፍርድ ተበይኖበት እንደነበር ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል፡፡
ለዛሬ ስኬቱ ወላጅ እናቱ ወይዘሮ ጎቴ ጎሎዶ ትልቅ ሚና እንደነበራቸው የሚናገረው የሕግ ምሩቅ÷ ክራንች እና ድጋፍ በማጣት በእጁና በደረቱ እየተንፏቀቀ ለረጅም ጊዜያት ትምህርት ቤት ሲመላለስ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ ዛሬ ግን ሁሉንም ታሪክ አድርጎታል፡፡
“ትምህርት ለማንም አይጠቅምም÷ እየተባለ ጫና ይደረግበት እንደነበር ይገልጻል፡፡
“አካል ጉዳተኞች ምንም ማድረግ እንደሚችሉ እኔ ምሳሌ ነኝ” የሚለው ባለታሪካችን ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት ዘርፍ 3 ነጥብ 3 የሆነ ውጤት በማስመዝገብ ተመርቋል።
በአስጨናቂ ጉዱ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!