Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 359 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስማረ መለሰ (ዶ/ር) ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተመራቂዎች በሰለጠኑበት የሙያ መስክ ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን በታማኝነትና በትጋት እንዲያገለግሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲው በተግባር ተኮር ትምህርትና ምርምር ግንባር ቀደም ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ራዕይ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ18ኛ ዙር መርሐ ግብር ካስመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 1ሺህ 108 የመጀመሪያ ዲግሪ እና 251 የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በሰላም አሰፋ

Exit mobile version