አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሚዛን ቴፒ እና ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመርቀዋል።
የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በ2ኛ ዲግሪ እንዲሁም በሌሎች መርሐ ግብሮች ያስተማራቸውን 701 ተማሪዎች ነው ያስመረቀው፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በመደበኛ እና ተከታታይ መርሐ ግብሮች በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 638 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በተስፋዬ ሚሬሳ