Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሀረሪ ክልል ካቢኔ የ2018 በጀት ከ7 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ እንዲሆን ወሰነ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት (ካቢኔ) የ2018 በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ረቂቅ በጀት 7 ቢሊየን 476 ሚሊየን ብር እንዲሆን ወስኗል፡፡

ካቢኔው በክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በቀረበለት ረቂቅ በጀት ላይ በመምከር ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

በዚህም ከተያዘው በጀት 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለካፒታል በጀት እንዲሁም 2 ቢሊየን 798 ሚሊየን ብር ለመደበኛ በጀት የሚውል ነው።

የበጀቱ ምንጭም በዋናነት በክልሉ ከተለያዩ ገቢዎች የሚሰበሰብ ገቢ እንዲሁም ከፌዴራል መንግሥት በፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀመር ለክልሎች የሚሰጥ ድጎማና ሌሎች ምንጮች ታሳቢ መደረጋቸው ተገልጿል።

የተያዘው በጀት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ28 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተመላክቷል።

በጀቱ በዋናነት ለዘላቂ ልማት ዘርፎች፣ የኑሮ ውድነትን ማረጋጋት በሚያስችሉና ምርታማነትን በሚያሳድጉ የግብርና ልማት ዘርፎች፣ ለስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ለገጠርና ከተማ ኮሪደር ልማት እንደሚውል ተጠቅሷል።

የገጠሩ ማህበረሰብን የመሰረት ልማት ጥያቄ ለመመለስ ለሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

በተስፋዬ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version