Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

43ኛው የጉሚ በለል መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 43ኛው የጉሚ በለል መድረክ “ባህላዊ ፍርድ ቤት ለማህበራዊ ፍትህ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ጋዛሊ አባሲመል፣ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

አቶ ጋዛሊ አባሲመል በመድረኩ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ የፍትሕ ሥርዓቱን ለማጠናከር ከባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ሁለቱ የፍትሕ ሥርዓቶች በትብብርና በቅንጅት እንዲሰሩ በማድረግ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እየተሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

አቶ ኃይሉ አዱኛ በበኩላቸው ÷ የባሕላዊ ዳኝነት ሥርዓት ለግጭት አፈታት ሒደት ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ ባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን ከዘመናዊ ፍርድ ቤቶች ጋር የማስተሳሰሩ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ በባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ጠቀሜታ ዙሪያ የተከናወኑ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

በጸሃይ ጉሉማ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Exit mobile version