Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ57 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተና ይወስዳሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተናን በኦንላይና እና በወረቀት ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል አለ የክልሉ ትምህርት ቢሮ፡፡

የቢሮው ሃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ እንዳሉት ÷ ተፈታኞች ከ481 የትምህርት ተቋማት የተወጣጡና በግል፣ በመንግስት፣ በርቀት እና በመደበኛ መርሐ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡

አጠቃላይ ተፈታኞቹ 57 ሺህ 19 ተማሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው÷ ከእነዚህ መካከልም 7 ሺህ 970 ተማሪዎች ፈተናውን በኦንላይን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡

ፈተናው በጂንካ፣ ዲላ፣ አርባ ምንጭና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሳውላ ካምፓስ እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡

የፈተና አስፈጻሚ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው ÷ፈተናው ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ወ/ሮ ፀሐይ ተማሪዎች የፈተናውን ሕግ በማክበር በተረጋጋ ሁኔታ መፈተን እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

በማቱሳላ ማቴዎስ

Exit mobile version