አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል፡፡
ተማሪዎቹ ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ለመውሰድ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ተዘጋጁ ማዕከላት እየገቡ ነው፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለፁት፤ ተፈታኞቹ በግል፣ በመንግስት፣ በርቀት እና በመደበኛ መርሃ ግብር በ481 ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
አጠቃላይ የተፈታኞች ቁጥር 57 ሺህ 19 መሆኑን ጠቁመው፤ ፈተናው በበይነ መረብ እና በወረቀት የሚሰጥ በመሆኑ ለተማሪዎች አዲስ እንዳይሆን የተግባር ልምምዶች መደረጋቸውንም አብራርተዋል።
ተማሪዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ የሚፈተኑ በመሆኑ ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የሥነ ልቦና ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል።
የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡
በማስተዋል አሰፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Documentary YouTube www.youtube.com/@fanamcdocumentary በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!