Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አረንጓዴ አሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሃሳብ በዳራ ኦቲልቾ ወረዳ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ከ307 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኞችን በ23 ሺህ 300 ሔክታር መሬት ላይ ለመትከል ዝግጅት ተጠናቅቆ ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸው÷ መርሐ ግብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ችግኝ መትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለሥራ እድል ፈጠራ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከልና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች እንዳሉት አስረድተዋል፡፡

ስለሆነም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ሕብረተሰቡ በመርሐ ግብሩ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና ይጫወታል የተተከሉ ችግኞች ጸድቀው የታቀደውን አላማ ያሳኩ ዘንድም ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበነት ሃላፊነት እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version